ክፍል 2: የምትወደው ምግብ ምንድነው ?

ክፍል 2: የምትወደው ምግብ ምንድነው ?

V
VOA Learning English
Dec 17, 2022

እንግሊዝኛን ከአና ጋር እንማር! የአሜሪካ እንግሊዝኛን ዕድሜአቸው ከ 8 እስከ 12 ዓመት ለሆነ ልጆች ማስተማሪያ አዲስ ኮርስ ነው።ትምህርቱ ከአማርኛ ጋር ጎን ለጎን በእንግሊዝኛ በሚካሄዱ ጥያቄና መልሶች፣ እንዲሁም በሚያዝናኑ አጋጣሚዎች የተሞላ ነው።

በተከታታይ ክፍሎች የተዘጋጀው ትምህርት በመሠረታዊ ቃላትና አባባሎች ይጀምርና ቀስ በቀስ በቀስ የመስማት፣ የመናገር የማንበብና የመፃፍድፍረትና መተማመንን እያዳበረ ይሄዳል። አድማጮች በአማርኛና በእንግሊዝኛ እየሰሙ እንዴት እንደሚባል እየደጋገሙ ይለማመዳሉ፤ሰዋሰውና ቃላትን ይፈትሻሉ፣ ይማራሉ፤ ወይም ደግሞ የሚያስደስቱና የሚያዝናኑ የእንግሊዝኛ ትምህርቶችን ዝም ብለው ማዳመጥ ይችላሉ።

መርኃግብሩ የሚያተኩረው ወጣት እንግሊዝኛ ተማሪዎች ላይ ቢሆንም ይዘቶቹ ቤተሰብ አብሮ ሆኖ ቢመለከታቸውና ቢከታተላቸውምየሚያስደስቱና የሚያነጋግሩ ናቸው። በአርባ ክፍሎች የተዘጋጁት ትምህርቶች ለመለማመጃ የሚሆኑ የሚታተሙ ገፆችና ለአስተማሪዎች፣ለወላጆችና ለአሳዳጊዎች የሚጠቅሙ የትምህርት ዕቅዶች አሏቸው።
https://learningenglish.voanews.com/p/8323.html

Comments are disabled for this video.